አዲስመጽሐፍበገበያ_ላይ

ከ 32 ሚሊዮን ኮፒ በላይ ከተሸጠው ከ RICH DAD POOR DAD መጽሐፍ ጸሐፊ ሮበርት ኪዮሳኪ አዲሱ #ሀብትየመገንባትጥበብ መጽሐፍ ላይ የተቀሰሙ 7 ጥበቦች፡-

1_የራስህንገንዘብአትም

የራስህን ገንዘብ ማተም ትችላለህ፡፡ ልክ ብሔራዊ ባንክ እንደሚያደርገው፡፡

ጥያቄው የገንዘብ ማብዥያ መሳሪያህ ምንድን ነው የሚሆነው? የሚለው ነው፡፡ ያንን ካወቅክ ብሔራዊ ባንክን ትሆናለህ፡፡ ሕጋዊ በሆነ መልክ የፈለግከውን ያህል ገንዘብ ማተም ትችላለህ፡፡ ሀብት የመገንባት ጥበብ መጽሐፍም እንዴት የራስህን ገንዘብ እንደምታትም ያስተምርሀል፡፡

2_ካፒታሊስት_ሁን

ሀብታሙ አባቴ ብዙ ጊዜ ይላል፣ “አብዛኞች የ “A” ተማሪዎች 2 + 2 = 4 የሆነውን ነገር ሁሉ ያውቃሉ፡፡ ነገር ግን አብዛኞች የ “A” ተማሪዎች ሁለት ሲደመር ሁለትን ወደ አራት ዶላር ወይም ወደ ሚሊዮኖች እንዴት እንደሚቀይሩ አያውቁም፡፡ ካፒታሊስቶች ማወቅ የሚፈልጉት 2+2= 4,000,000 እንዴት እንደሚሆን ነው፡፡ ይህን አይነት ሂሳብ ነው ካፒታሊስቶች ሊያጠኑት የሚፈልጉት፡፡

3_ስራፈጣሪሁን!

የወደፊቱ ዓለም በትክክል በቤቶቻችን፣ በልቦቻችን እና በልጆቻችን አእምሮዎች ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ሁላችንም በሰው ልጅ ታሪክ እጅግ ከፍተኛ ለውጥ የምናካሄድበት ወቅት እና ሁኔታ ላይ ነን ብዬ አምናለሁ፡፡

ቀውሶች ሊቀጥሉ ይችላሉ? አዎን፡፡ ግጭቶች ሊኖሩ ይችላሉ? ምናልባት፡፡ ፍርሃት እና ስጋት ሊኖር ይችላል? አዎን፡፡ አዳዲስ ስራ ፈጣሪዎች አሸናፊ ሆነው በመውጣት ዕድሎችን ይወስዳሉ? በእርግጠኝነት አዎን፡፡ ስለዚህ ስራ ፈጣሪ መሆን አለብህ!

4_ሀብትየመገንባትቅመሞች

መበረታታት (Inspire) የሚለው ቃል የመጣው ከላቲን “ispiratio” ሲሆን “በመንፈስ ሆነ ወይም በእግዚአብሔር ጠነከረ” ማለት ነው፡፡ መነቃቃት (Motivate) የሚለው ቃል የመጣው ከላቲን “motere” ሲሆን ወደፊት መንቀሳቀስ ማለት ነው፡፡ መበረታታት እና መነቃቃት ሀብት የመገንባት ቅመሞች ናቸው፡፡

5_ትምህርትብቻውንሀብታም_አያደርግም

የሆነ ሰው፣ ለገንዘብ ችግሩ መፍትሔ እንዲሆን “ተጨማሪ ዲግሪ ለመስራት ልማር ነው” ሲል ስሰማ በምፀት ጥርሴን እነክሳለሁ፡፡

“ትምህርት ቤት መማር ሀብታም ካደረገ፣ የትምህርት ቤት መምህራን ሚሊየነሮች ይሆኑ ነበር” ብሎ ሀብታሙ አባቴ ሲናገር እስከ አሁን ይሰማኛል፡፡ ሀብታም የምትሆነው ስለ ሀብት በማጥናትና በመተግበር ነው- እሱን ደግሞ ትምህርት ቤቶች አያስተምሩህም፡፡

6_እያስገባህነውወይስ_እያወጣህ?

ሀብታሙ አባቴ “ሀብት” የሚለውን በቀላሉ ተርጉሞታል፡- “ወደ ኪሴ ገንዘብ የሚያስገባ ነገር፡፡” “እዳ” የሚለው የእርሱ ቀላል ትርጓሜ፡- “ገንዘብ ከኪሴ የሚወስድ ነገር፡፡” ምን እያደረግክ ነው? እያስገባህ ነው እያወጣህ?

7_መብትህ_ነው

ሕይወትህን መቀየር ከፈለግክ፣ ሁናቴህን ቀይር፤ የምትሰራበትን የገቢ አይነት ለመቀየር ተማር፡፡ እንዲሁም ነጻ ፈቃድ እንዳለህ አስታውስ፡፡ ድሀ ሆነህ መኖር ከፈለግክ መብትህ ነው፡፡ ሀብታም መሆንም ከፈለግክ መብትህ ነው፡፡ “ለመዘመር መማር እስካልፈለገ ድረስ ጉጉትን እንዲዘምር ለማስተማር አትሞክር!”

Source RICH DAD POOR DAD

Leave a Reply

%d bloggers like this: