“አያ ናይዝጊ” እንጂ “አያና እግዚአ” የሚባል መሪ አልነበረም!

By: THE TIGRAY INTERCEPT

የትግራይ ግዛት ለክፍለ ዘመናት እስከ እምባ ጊዩርጊስ (ዳባትን አልፈህ እስከ ጎንደር አካባቢ) ድረስ የነበረ መሆኑን በቂ የታሪክ ማስረጃዎች አሉን:: ቢሆንም የአማራ ተስፋፊ ሀይል በሕግ: በስርዓት እና በታሪክ ማስረጃ ሳይሆን እንደ ፍላጎቱ በሀይል አስተማሪ ቅጣት በመቅጣት በጉልበት ግዛታችንን እናስመልሳለን::

ታሪክ መስራት የማይችሉ ነገር ግን የታሪክ ዘራፊዎቹ የአማራ ተስፋፊ ሀይሎች የትግራዋይ ንጉስ ታሪኩ አይደለም የሰራውን ቤተመንግስት ስሙን እንኳን በአግባቡ አያውቁትም:: አያ ማለት በትግርኛ አባት ማለት ነው:: ናይዝጊ (ናይ እዝጊ) ማለት ደግሞ “የእግዚአብሔር” ማለት ሲሆን ይህ ስም የትግርኛ ተናጋሪ ስም ነው:: ደጃዝማች ናይዝጊ ከአባታቸው ዘሚካኤል እናታቸው ዝሕለት በእምባ ቀታ በሚባል አካባቢ ነው የተወለዱት::

አያ ናይዝጊ በትግራዋዩ ደጃዝማች ሙሉ በጦርነት ከተሸነፉበት ወቅት በፊት አጠቃላይ የትግራይ ትግሪኚ አካባቢዎች ገዢ ነበሩ:: በጦርነት ተሸንፈው ከ9 አመታት እስራት በኃላ በአፄ በካፋ የጎንደሩ (ኦሮሞ ነው) “በጎንደር ዘመነ መንግስት” ትእዛዝ እንዲፈቱ ሲደረጉ የቆላው ወልቃይት መዘጋ ገዢ ሆኑ:: የደጃዝማች ናይዝጊ ግዛት በሰሜን እስከ ተከዘ: በደቡብ እስከ ወገራ እና ጥቅል ድንጋይ: በምብራቕ እስከ ተከዘ: በምዕራብ እስከ ገዳሪፍ በአጠቃላይ 9 አውራጃዎች ለ40 አመታት አስተዳድሯል:: ልጆቹ “ስራሕ ክርስቶስ” እንዲሁም “ቃል ክርስቶስ” አባታቸው በመተካት ወልቃይትን አስተዳድረዋል::

ይህ ቤተመንግስት “ቤት ሙሉ” እየትባለ የሚታወቅ ሲሆን በማይ ጋባ ምዕራብ ትግራይ ላይ ነው የሚገኘው::

ኦሮሞ ንጉስ በጎንደር ዘመነ መንግስት ነበር እንዴ ለምትሉ ደግሞ የኢኮነሚስቱ: ወታደራዊ አመራር: ፓለቲከኛ እና የታሪክ ተማራማሪው ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ ንግግር እናስታውሶት:-

“ትምክህተኛ የኢትዮጵያን ታሪክ የተጠበቀው: እንክብካቤ የተደረገለት በአማራ ብቻ ነው ብሎ ነው የሚያስቀምጠው:: የጎንደር ታሪክ ሲያነሳ የአማራ ታሪክ ብቻ ነው የሚያነሳው: ኦሮሞውን አያነሳም:: ፋሲለደስን ብቻ ነው የሚያነሳው በካፋን አያነሳም:: አፄ በካፋ ኦሮምኛ ተናጋሪ ነው ተብሎ ስለሚገለፅ ነው:: ስለ አፄ ሲሲኒዮስ ሲያወራ የኦሮሞ አባዱላ የነበረ መሆኑን አያወራም:: የመጫ ኦሮሞዎች መርቶ ጅማን የተቆጣጠረው ሲሲኒዮስ መሆኑን አይናገርም:: የራስ መኮንን አባት ወይም የአፄ ሃይለስላሴ አያት ኦሮሞ መሆናቸውም አይናገርም::

እቴጌ ጣይቱን እንጦጦ ላይ ያሰራቸው ማን ነው ቢባል ፊታውራሪ ሃብተጊዮርጊስ ነው:: ሃብተጊዮርጊስ የት ነው ቢባል ኦሮሞ ነው:: ሰገሌ ጦርነት ላይ ተዋግቶ የሰሜን ሸዋ መሳፍንት በሰሜን ኢትዮጵያ መሳፍንት የበላይነት እንዲኖራቸው ያደረገው በአብዛኛው የምዕራብ ሸዋ እና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ተዋጊ ነው::

ሰሜን ያለው ኦሮሞ በጎንደር ዘመነ መንግስት ተቀላቅሏል:: ንጉስ እስከ መሆንም ደርሷል:: ሰሜን ሸዋ ያለው ኦሮሞ ቀድሞ ተቀላቅሏል:: አርሲ ያለው ደግሞ ወደኃላ ነው የተቀላቀለው:: (ወደ ኢትዮጵያ)”

Leave a Reply

%d bloggers like this: